ቤዛ ፡ ሆኖልናል (Beza Honolenal) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

ጨለማው ተገፏል ፅልመት ተወግዷል
ፍርሃት ጭንቀት ሄዷል ጌታ ደርሶልናል
በሞት ጥላ ላለን ብርሃን በርቶልናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ሆኖልናል

የሞት መውጊያው መሳሪያው - ተሰበረ መንደፊያው
የዲያብሎስን ስራ ሊያፈርስ - ተገለጠ ጌታ ኢየሱስ
የሃጢያትን ጉልበት ሊያፈርስ - ተገለጠ ጌታ ኢየሱስ

ጨለማው ተገፏል....

የሞት ሽታ የሞት ጠረን - ትናንትና ከቦን ነበር
ዛሬ ብርሃን በርቶልናል - የእግዚአብሄር ልጅ ደርሶልናል

ጨለማው ተገፏል....

የእሳቱ ኃይል ጥንካሬው - እጅግ ቢከብድ ቢደርስ ሰማይ
ልጁን ልኮ አውጥቶናል - ከሳቱ ሃይል አድኖናል