አመልክሃለሁ (2) (Amelkehalehu (2)) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:00
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

አንት ከከበርክ እኔ ምን እሻለሁ
ያንተ መክበር ያ የኔ ደስታ ነው
ዘላለም አመልክሃለሁ
ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ

        ድምፅህን ስሰማው እጅግ ደስ ይለኛል
        ሽር ጉድ ስልልህ ክብር ይሰማኛል
        ረሃቤም ጥማቴም ፈቃድህን ማድረግ ነው
        ፃድቁን አይቼ ጠግቤ መኖር ነው

ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ /4/

            ሙሽራው ሲከብር ደስ እንዲለው ሚዜ
           ደስታዬ ይሞላል ከብረህ ሳይህ ጊዜ
           ድመቅ በሁሉ ላይ ታይልኝ ቀን ሙሉ
           ፍጥረታት ሁሉ አይተው ጌታዬ ይበሉ

ክብር ይሁን በላይ ክብር ይሁን በሰማይ
በፍጥረት ሁሉ ላይ አንተ ብቻህን ታይ
ክብር ይሁን በታች ክብር ይሁን በምድር
በእጆች ስራ ላይ አንተ ብቻ ክበር

ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ /4/