ክብሬ (Kebrie) - አስማማው ፡ ቢረሳው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስማማው ፡ ቢረሳው
(Asmamaw Biresaw)

Asmamaw Biresaw 1.jpg


(1)

የመኖር ፡ ምክንያቴ
(Yemenor Mikniate)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስማማው ፡ ቢረሳው ፡ አልበሞች
(Albums by Asmamaw Biresaw)

{ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ
ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X)

ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ
በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ
{አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X)

አስመልጦኛል ፡ ታሪክን ፡ ሠርቶ
በቀራንዮ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፍሎ
ታዲያ ፡ ለኢየሱስ ፡ ለሆነኝ ፡ ሕይወት
መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት?
    {ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ
      ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ
      በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X)
ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ
በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ
  {አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X)
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ክብር
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ አምልኮ
ይገባሃል ፡ ስግደት
ይገባሃል ፡ አምልኮ
ለዘለዓለም ፡ ክበር
ክበር ፡ ለዘለዓለም ።

ሸክሜ ፡ ከላዬ ፣ ተንከባለለ
ይኸው ፡ ዛሬማ ፣ ቀና ፡ ብያለሁ
ተቀይሮልኝ ፡ ሁሉ ፡ ታሪኬ
ዕጣ ፡ ደረሰኝ ፡ ሆንከኝ ፡ አምላኬ ።
    {ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ
      ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ
      በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X)
ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ
በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ
  {አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ
  አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X)