አንተ ፡ የእኔ (Ante Yenie) - አስማማው ፡ ቢረሳው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስማማው ፡ ቢረሳው
(Asmamaw Biresaw)

Asmamaw Biresaw 1.jpg


(1)

የመኖር ፡ ምክንያቴ
(Yemenor Mekniyatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስማማው ፡ ቢረሳው ፡ አልበሞች
(Albums by Asmamaw Biresaw)

አሃ! አሃሃ! (፪x)

በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል
በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አስፍሮኛል
አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል (፪x)

አዝ፦ አዎ! እኔ ፡ የእርሱ
አዎ! እርሱም ፡ የእኔ
አዎ! የማገኘው
አዎ! ሁሌ ፡ ከጐኔ (፪x)

አሃ! አሃሃ! (፪x)

የከበረ ፡ ዋጋ ፡ ተከፍሎልኝ
በደሙ ፡ የተገኘሁ ፡ ልጁ ፡ ነኝ
አይደለም ፡ ጠላቴ ፡ እንደሚለው
መላው ፡ እኔነቴ ፡ የእርሱ ፡ ነው

የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ
የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ
ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ

ዓላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለው
ከሚያደርገው ፡ ነገር ፡ የማየው
እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ፡ የሚጠብቀኝ
ማን ፡ እንደርሱ ፡ ለእኔ ፡ ሊሆንልኝ

የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ
የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ
ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ

በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል
በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አስፍሮኛል
አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል (፪x)

አዝ፦ አዎ! እኔ ፡ የእርሱ
አዎ! እርሱም ፡ የእኔ
አዎ! የማገኘው
አዎ! ሁሌ ፡ ከጐኔ (፪x)

አሃ! አሃሃ! (፪x)

ውብና ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ የፈጠረኝ
ለምሥጋናው ፡ ለአምልኮ ፡ ያጨኝ
የተፈጠርኩበት ፡ ውድ ፡ ዓላማ
ስለገባኝ ፡ ለእኔ
ሌላ ፡ አልሰማም

የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ
የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ
ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም ፡ አይችልም
ሊነጥለኝ