አጋፔ (Agape) - አሸናፊ ፡ በስር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አሸናፊ ፡ በስር
(Ashenafi Besir)

Ashenafi Besir 1.jpg


(1)

የልቤ ፡ መሻት
(Yelebie Meshat)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2015)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሸናፊ ፡ በስር ፡ አልበሞች
(Albums by Ashenafi Besir)

አንድ ፡ ጉዳይ ፡ አንድ ፡ ነገር
ሲወራ ፡ ቢዋል ፡ ሲተረክ ፡ ቢታደር
የማያሰለች ፡ እውነት ፡ የሆነ ፡
ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ የተከወነ (፪x)

አዝአጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ
ሞተልን ፡ ሳይራራ ፡ ለነፍሱ
አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ
ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ንጉሡ

እጆች ፡ ገረፉት ፡ የፈጠራቸው
ተፉበት ፡ ጌታ ፡ ላይ ፡ መች ፡ ፀፀታቸው
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ጩኽቱስ ፡ ተሰማ
የዓለሙ ፡ ጌታ ፡ ሆነ ፡ እንደ ፡ ደካማ

ንጹህ ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ እንደወንጀለኛ
በውርደት ፡ ሰቀሉት ፡ የሱስን ፡ ስለኛ
መለኪያስ ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለዚህ ፡ ፍቅር ፡ መጠን
እንዲሁ ፡ ወዶን ፡ እራሱን ፡ ለሰጠን

አዝአጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ
ሞተልን ፡ ሳይራራ ፡ ለነፍሱ
አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ
ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ንጉሡ

በዚህ ፡ ዓለም ፡ ፍቅር (፪x)
የወደደውን ፡ ማንም ፡ ይወዳል
መልካም ፡ ላረገ ፡ እርሱም ፡ ይክሳል
የኢየሱሴ ፡ ግን ፡ የሚለየው
ራሱን ፡ የሰጠ ፡ ለጠላ ፡ ነው
የኢየሱሴማ ፡ የሚለየው
ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ለገፋው ፡ ነው