From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
መሰዊያዬን ፡ ልስራ ፡ ከማጠኔ ፡ በፊት
ከድንኳኔ ፡ ላውጣ ፡ አንተ ፡ የማትከብርበትን ፡ አዎ
እንጨቴን ፡ ልረብርብ ፡ አንድደው ፡ እሳቴን
መስዕዋት ፡ አድርጌ ፡ ላስቀምጠው ፡ እራሴን (፪x)
አንተን ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ አምልኮዬ
አንተን ፡ ካከበረህ ፡ ኑሮዬ
ክበርልኝ ፡ ጌታዬ (፪x)
ክበርበት ፡ ጌታዬ (፪x)
የመኖሬ ፡ ሚስጥር ፡ የመክበሬ ፡ ጅምር
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ እግዚአብሔር (፬x)
የእኔ ፡ ከፍታዬ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x)
የእኔ ፡ የብቻዬ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x)
መከበሪያዬ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x)
የእኔ ፡ ማረፊያዬ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x)
ሰማይን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ
ምድርንም ፡ በቃልህ ፡ ያፀናህ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፬x)
አላክብር ፡ አላምልክ
የልቤ ፡ ጌታ ፡ ነህ
አላርክ ፡ አላነግሥ
የቤቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ
ላይ ፡ በሰማይ ፡ በዙፋንህ ፡ ሆነህ
በምድር ፡ ያለውን ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
|