ትዝ ፡ ይለኛል (Tez Yelegnal) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 3.jpg


(3)

ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም
(Telant Zarie Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

ትላንትን ፡ ሳስበው ፡ በዛሬ ፡ ላይ ፡ ሆኜ
ስንቱን ፡ አልፊያለሁ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ መክሬ (፪x)
ምንድን ፡ ነው ፡ ስል ፡ እንደዚህ ፡ ያቆመኝ
ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ትዝ ፡ የሚለኝ
አባት ፡ መሆንህ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ትዝ ፡ የሚለኝ

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ያነባ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የጣለ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ አንተ ፡ ሞትህ ፡ ለእኔ ፡ እኔን ፡ ልታኖር
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ መነሻ ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲህ ፡ የወደድከኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ ያስጣለኝ (፪x)

ለካስ ፡ ልክ ፡ ነበር ፡ ስትነግረኝም ፡ ያኔ
ዛሬ ፡ ደርሼበት ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ (፪x)
አላማርርህም ፡ ሳስብ ፡ መፈጠሬን
ለእኔ ፡ ተስማምቶኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መኖሬ (፪x)

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ያነባ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የጣለ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ አንተ ፡ ሞትህ ፡ ለእኔ ፡ እኔን ፡ ልታኖር
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ መነሻ ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲህ ፡ የወደድከኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ ያስጣለኝ

ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ርህሩሁን ፡ አብርደህ ፡ በረድ ፡ ስታኖረኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እንደ ፡ አባት ፡ ሆነህ ፡ መክረህ ፡ ያሳደከኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያንን ፡ ምድረበዳ ፡ በአንተ ፡ ያለፍኩበት
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት

ነፋሱም ፡ ሳይነፍስ ፡ አይኖርም ፡ ደመና
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ ተቀበልኩህና (፪x)
ስለ ፡ አንተ ፡ ሲወራ ፡ ከሩቁ ፡ ሰምቼ
ቀርቤ ፡ አየሁኝ ፡ ማዳንን ፡ በዓይኖቼ
አባት ፡ መሆንህን ፡ አየሁኝ ፡ በዓይኖቼ

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ርህሩሁን ፡ አብርደህ ፡ በረድ ፡ ስታኖረኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እንደ ፡ አባት ፡ ሆነህ ፡ መክረህ ፡ ያሳደከኝ
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያንን ፡ ምድረበዳ ፡ በአንተ ፡ ያለፍኩበት
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት (፪x)