ትላንት ፡ ተብሎ (Telant Tebelo) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 3.jpg


(3)

ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም
(Telant Zarie Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

አዝ፦ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ ዛሬ ፡ ሊጠራ
አሳልፎት ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ በተራ
አምላኬን ፡ እንዲህ ፡ በሉልኝ ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
እርሱ ፡ በሰራልኝ ፡ ተዓምራት/ቀናቶች ፡ እኔ ፡ ኖራለሁ (፪x)

ልዩነት ፡ አምጥቶ ፡ ሌሊቱ
ለጠላቴ ፡ ሆነ ፡ ውድቀቱ
ሊያጠፋኝ ፡ ነበረ ፡ ምኞቱ
እንዲሁ ፡ ደከመ ፡ በከንቱ

እኔማ ፡ አምልጫለሁ ፡ ወጥመዴ ፡ ተሰብሮ
ጠላቴ ፡ ላይደግም ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ጥሎ
እኔማ ፡ አምልጫለሁ ፡ ወጥመዴ ፡ ተሰብሮ
ጠላቴ ፡ ላይደግም ፡ ከእግሬ ፡ በታች ፡ ጥሎ

ይጨምራል ፡ ገና ፡ ሙሉ ፡ ቀን ፡ እስኪሆን (፪x)
የአምላኬን ፡ ተዓምራት ፡ አያለሁ ፡ ማዳኑን (፪x)
ለነገም ፡ ለዛሬ ፡ ምላሽ ፡ አለው ፡ ጌታ
በጭራሽ ፡ አልወርድም ፡ እኔ ፡ ከአየልኝ ፡ ከፍታ

አዝ፦ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ ዛሬ ፡ ሊጠራ
አሳልፎት ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ በተራ
አምላኬን ፡ እንዲህ ፡ በሉልኝ ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
እርሱ ፡ በሰራልኝ ፡ ተዓምራት/ቀናቶች ፡ እኔ ፡ ኖራለሁ (፫x)

ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)
ቀኑ ፡ ክፉ ፡ ቢሆን ፡ ነግሬው ፡ አልፋለሁ (፪x)
በሞት ፡ ጥላ ፡ ብሄድ ፡ መቼ ፡ ያስፈራኛል
ሰባሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ወጥቶልኛል (፪x)