ከፍታዬን ፡ ልያዝ (Kefetayien Leyaz) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 3.jpg


(3)

ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም
(Telant Zarie Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

የጠላቶች ፡ ቁጣ ፡ ቢነድም ፡ በላዪ
ከእነርሱ ፡ ይበልጣል ፡ አዎ ፡ የጠራኝ ፡ ጌታዬ
ልቤም ፡ አይደነግጥ ፡ በወጀቡ ፡ ብዛት
መንገድ ፡ ላይ ፡ አይጥለኝም ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የታመንኩበት (፪x)

ወጀቡን ፡ አይቼ ፡ ፀጋዬን ፡ አልጥልም
የከበረውን ፡ ነገር ፡ አዎ ፡ ለውሾች ፡ አልሰጥም
እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፡ አይላላም
በጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ እኔ ፡ ስፍራዬን ፡ አልለቅም (፪x)

ከፍታዬን ፡ ልያዝ ፡ ተራራውን
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ያየልኝን
አልደከምኩም ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ
የሰማሁት ፡ ወንጌል ፡ አላረጀም (፪x)

ዮርዳኖስን ፡ አይተው ፡ እህ ፡ ሰዎች ፡ ብዙ ፡ ቢሉ
እኔ ፡ እሻገራለሁ ፡ ሰምቻለሁ ፡ ቃሉን ፡ አዬ
ሰምቻለሁ ፡ ቃሉን
ካየልኝ ፡ በረከት ፡ እህ ፡ ከግቤ ፡ ላይ ፡ ሳልደርስ ፡ ኦሆ
ወጀቡን ፡ አይቼ ፡ እኔስ ፡ አልመለስም ፡ አዬ
እኔስ ፡ አልመለስም

እልፍ ፡ በል ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
መንገዴን ፡ ጀምሬ ፡ እንዴት ፡ እመለሳለሁ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል
ልቤም ፡ ላይደነግጥ ፡ ይህን ፡ ቃል ፡ አምኖታል

ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ እህ ፡ ብዬ ፡ አልጠራጠር ፡ ኦሆ
እግዚአብሔር ፡ ከሰጠኝ ፡ ተራራማውን ፡ አገር
አዬ ፡ ተራራማውን ፡ አገር
ፈርቼ ፡ አልመለስም ፡ እህ ፡ ረጃጅሞቹን ፡ ኦሆ
እገጥማቸዋለሁ ፡ ጠርቼው ፡ አምላኬን
አሄ ፡ ጠርቼው ፡ አምላኬን

እልፍ ፡ በል ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
መንገዴን ፡ ጀምሬ ፡ እንዴት ፡ እመለሳለሁ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል
ልቤም ፡ ላይደነግጥ ፡ ይህን ፡ ቃል ፡ አምኖታል