ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ (Hazenien Bante Teyalehu) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 3.jpg


(3)

ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም
(Telant Zarie Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

በምንም ፡ አልሰጋም ፡ ልቤም ፡ አይደነግጥ
በሆነው ፡ ባልሆነው ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ መናወጥ
ስለ ፡ ነገ ፡ እያሰብኩ ፡ እኔ ፡ አልጨነቅም
እግዚአብሔር ፡ ሳያውቀው ፡ በእኔ ፡ የሚሆን ፡ የለም

አዝ፦ እኔማ
ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ
ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ (፪x)

ለማይሞልውና ፡ ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ታዲያ ፡ ለምንድን ፡ ነው ፡ መጨነቅ ፡ መሸበር
ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
ጠላት ፡ ይስማው ፡ እንጂ ፡ ድሌን ፡ ዘምራለሁ

አዝ፦ እኔማ
ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ
ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ

ምክኒያቱ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ዛሬን ፡ ለመኖሬ
ስንቱን ፡ በእርሱ ፡ አልፌ ፡ ስንቱን ፡ ተሻግሬ
እግዚአብሔር ፡ ስላለኝ ፡ ነገንም ፡ ደፍራለሁ
ዘመኑን ፡ ዋጅቼ ፡ በቀኑ ፡ ኖራለሁ

አዝ፦ እኔማ
ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ
ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ
ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ

ነፍሴ ፡ አትማረሪ ፡ አታስጨንቂኝ
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ የሚሆንልኝ
በሰው ፡ አልታመን ፡ እኮ ፡ ሥጋ ፡ ለባሹን
ጌታ ፡ ይሰጠኛል ፡ መከናወኔን

እ ፡ ነፍሴ ፡ አትማረሪ
እ ፡ አታስጨንቂኝ
እ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው
ተዪኝ ፡ የሚሆንልኝ
እ ፡ በሰው ፡ አልታመንኩ
እ ፡ ሥጋ ፡ ለባሹን
እ ፡ ጌታ ፡ ይሰጠኛል
ተዪኝ ፡ መከናወኔን