አንተ ፡ ነህ ፡ አባቴ (Ante Neh Abatie) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 3.jpg


(3)

ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም
(Telant Zarie Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

ሰው ፡ እንዳለህ ፡ አይደለህም ፡ አእምሮ ፡ እንዳሰበህ
ከመጣው ፡ ሁሉ ፡ ታልፋለህ ፡ ከተነገረልህ (፪x)

ከሚሉህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ
ከሚሉህ ፡ በላይ
ከሚሉህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ አምላኬ
ከሚሉህ ፡ በላይ (፪x)

ብዙዎች ፡ አውቀናል ፡ እንዳሉ
በራሳቸው ፡ አእምሮ ፡ እንዳሰሉ
አንተ ፡ ግን ፡ እንደዛ ፡ አይደለህም
ትልቅ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ አያውቅህም
አስገረመኝና ፡ ሥራህ
ማልጄ ፡ ተነሳሁ ፡ ላመልክህ
ፈቃዴን ፡ ሰጠሁ ፡ እራሴን
ግዛኝ ፡ ኢየሱሴ

ግዛኝ ፡ ኢየሱሴ (፰x)

አላፋው ፡ አግዳሚው ፡ እንዳለህ
አውቀናል ፡ ብለው ፡ እንዳወሩ
ሺህ ፡ ቃል ፡ ቢደረደር ፡ አይገልፅህ
አምላኬ ፡ ከመባል ፡ ታልፋለህ
በትላንቱ ፡ ነገር ፡ ስገረም
ዛሬም ፡ አስደነቅከኝ ፡ ዳግም
ተዓምራትህ ፡ በዛ ፡ በሕይወቴ
አንተ ፡ ነህ ፡ አባቴ

አንተ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፲x)

እስከመቼ ፡ ያልኩኝ ፡ ፍቺ ፡ ላጣው ፡ ህልሜ
ምላሽን ፡ ሰጥቶኛል ፡ እንዳልቀር ፡ ደክሜ
ጌታ ፡ ባየኝ ፡ ወራት ፡ እንዲህ ፡ ሆኖልኛል
አንደበቴም ፡ ሁሉ ፡ ዛሬማ ፡ ምሥጋናን ፡ ያወራል

ዘመርኩበት ፡ ባለቀስኩበት
ዘመርኩበት ፡ አይሆንም ፡ ባልኩበት
ዘመርኩበት ፡ ባጉረመረምኩበት
ዘመርኩበት ፡ በጠላቶቼ ፡ ፊት (፫x)

ምንም ፡ ታናሽ ፡ ቢሆን ፡ ጅማሬው ፡ የተነሳበት
ፍፃሜው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ በአምላኩ ፡ የሚደርስበት
እጅህን ፡ አታንሳ ፡ በድፍረት ፡ ጌታ ፡ በገባው ፡ ላይ
ስለ ፡ እርሱ ፡ ተዋጊ ፡ ተሟጋች ፡ አለና ፡ በሰማይ (፪x)