አንተ ፡ ለኔ መልካም ነህ (Ante lene melkam neh) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

Asfaw Melese 4.jpg


(4)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

[ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ቢዋሹ
እኔ ግን አልልም ከእነርሱ እንደ አንዱ] 2

[አቤቱ ሥርዓትህ መካሪ ነው
ምስክርነትህ ተድላዬ] 2

የጠላቶች ቁጣ በነደደ ጊዜ
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2
የሰው ፊት ሲጠቁር ጊዜ ሲለውጠው
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2
ገዢዎች በእኔ ላይ በተነሱ ሰዓት
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2

ዘመኑ ሲከፋ ቀኑ ሲጨላልም
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2
አለቆች በእኔ ላይ በዋሹብኝ ሰዓት
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2
ምድረ በዳ ሲሆን የሚታየው ነገር
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2

የማይነጋ መስሎ የጨለመው
የጠላቴ ቁጣ ድንፋታው
ከፍታዬን ጌታ ሲጨምር
አድርጎኛል ለጠላት ሽብር
አድርጎኛል ለሰይጣን ሽብር
ምክንያቱ ነኝ ለጠላት ሽብር

የትላንቱ ዛሬ የት አለ?
ሊያጠፋኝ የተማማለ
ምኞት ሆኖ ቀረ ሃሳቡ
እኔስ አለሁ ዛሬም በቤቱ /3

[ተማምኜሃለሁ በምንም አልሰጋም
ተደግፌሃለሁ እኔ አልናወጥም] 2

ወጀቡ ሲበዛ ሠልፉ ሲበረታ
[አንተ ለእኔ መልካም ነህ
አንተ ለእኔ መልካም] 2
[ጌታ ለእኔ መልካም ነህ
ጌታ ለእኔ መልካም] 2