Art Minitsry Hallelujah Choir

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በምስጋና ላይ እጨምራለው ምስጋናx2 ፍቅሩ ማርኮኛል ምህረቱ ያዘምረኛልx2

አቤቱ አምላኬ ሆይ ለሃይልህ እቀኛለው ጠዋት ማታ ሁሌ ላንተ ክብርን እሰጣለው በምህረቱ ያመውቀው ጌታ ደስ ደስ ይለኛል

ምህረትህ ስላቆመኝ አመስግኚ ይለኛል

ዛሬም እጨምራለው የኔ ጌታ ክበር ነገም እጨምራለው የኔ ጌታ ንገስx2

በምስጋና ላይ እጨምራለው ምስጋናx2 ፍቅሩ ማርኮኛል ምህረቱ ያዘምረኛልx2

ነብሴ ከሞት አይኔን ከእንባ አድነሃልና ስሜን በህይወት መዝገብ ፅፈሕልኛልና ያረክልኝን እኔ እያሰብኩ ስለ አንተ አወራለው ማርኮኝ ስለያዘኝ ፍቅርክ አዜምለሀለው

ዛሬም እጨምራለው የኔ ጌታ ክበር ነገም እጨምራለው የኔ ጌታ ንገስx2

በምስጋና ላይ እጨምራለው ምስጋናx2 ፍቅሩ ማርኮኛል ምህረቱ ያዘምረኛልx2

ነብሴ ከሞት አይኔን ከእንባ አድነሃልና ስሜን በህይወት መዝገብ ፅፈሕልኛና ያረክልኝን እኔ እያሰብኩ ስለ አንተ አወራለው ማርኮኝ ስለያዘኝ ፍቅርክ አዜምለሀለው

ዛሬም እጨምራለው የኔ ጌታ ክበር ነገም እጨምራለው የኔ ጌታ ንገስx2

እስከ አለም ፍጻሜ ከናተ ጋር እሆናለው ብለህ እንደተናገርክ ቃልክን ፈጸምከው በተራራ ቢሆን ደግሞ እሸለቆ

አብረኧኝ ሆነሃል አማኑኤል

እንደስምህ እኛም አይተንሃል ጌታ ነህ እንደስምህ አዳኝ ነህ እንደስምህ ገናና እንደስምህx2አሜንx4

ሰላሳ ስምንት አመት አልጋላይ የተኛውን ሰው የለኝም ብሎ ተስፋ የቆረጠውን ያለህበት ድረስ ሄደህ ፈውሰሃል አዳኝ ነህ የኛ ጌታ እየሱስ እንደስምህ እኛም አይተንሃል አዳኝ ነህ እንደስምህ ፈዋሽ ነህ እንደስምህ ገናና እንደስምህx2አሜንx2

ከስም ሁሉ በላይ ስም ተሰቶሃል የሲኦልን ቁልፍ በእጅህ ይዘሃል ፍጥረታትም ሁሉ ይበረከካሉ ለታላቁ ስምህ ክብርን ይሰጣሉ

ጌታ ነህ እንደስምህ አምላክ ነህ እንደስምህ ገናና እንደስምህx2አሜንx4