ማልጄ ፡ ልነሳ (Malejie Lenesa) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይጮሃል
ጆሮም ፡ አልሰጠው ፡ ይደክማል
ለእኔ ፡ የሆነልኝ ፡ እንደዚህ ፡ ነው
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደርሶ ፡ ወይን ፡ አብቦልኝ ፡ ነው (፪x)

በለሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል
ጌታውን ፡ የጠበቀ ፡ ይከብራል
ከአምላኩን ፡ ተማምኖ ፡ የከሰረ ፡ የታል
በጊዜው ፡ ሰዓቱ ፡ ሁሉ ፡ አምሮለታል (፪x)

ማልጄ ፡ ልነሳ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣ
አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ላሰማ ፡ የድል ፡ ዜማ
አስጨናቂው ፡ ለሊት ፡ አልፎልኛል
ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ በርቶልኛል (፪x)

ውሎ ፡ የማድር ፡ ብሆን ፡ ከንጉሥ ፡ ደጅ ፡ አፍ
ክፉ ፡ የሚታሰበ ፡ ከንጉሥ ፡ ወዳጅ
ጌታውን ፡ ለጠበቀ ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ
በክፉው ፡ ምክር ፡ ላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተገለጠ (፪x)

ማልጄ ፡ ልነሳ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣ
አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ላሰማ ፡ የድል ፡ ዜማ
አስጨናቂው ፡ ለሊት ፡ አልፎልኛል
ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ በርቶልኛል (፪x)