ለምን (Lemen) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

በጊዜያዊው ፡ ነገር ፡ ልቤ ፡ እንዳይሸነፍ
በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ነፍሴ ፡ እንዳትታለፍ
ቃልህን ፡ በልቤ ፡ ሰውረው ፡ ጌታዬ
ትዛዝህን ፡ ልጠብቅ
ማስተዋል ፡ ይሁነኝ ፡ ወዳጄ
ጥበብህ ፡ ትሁነኝ ፡ እህቴ (፪x)

ያንተውማ ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ይይዘኛል
የሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ያታልለኛል
ከንቱውማ ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ይይዘኛል
የሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ያታልለኛል

ለምን ፡ ለምን ፡ አሄሄ (፪x)

ትላንትና ፡ የናቁትን
ከንቱ ፡ ብዬ ፡ ያጥላላሁትን
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ልወዳጀው
ለምንድን ፡ ነው ፡ እንዲህ
ፍቅር/ጓደኛ ፡ እምሆን (፪x)

ባሞግስህ ፡ ደግሞ ፡ መልሶ ፡ ሲያሟግ
ባከበርህ ፡ ደግሞ ፡ ሲያማርርብኝ
ክፉ ፡ ደጉን ፡ ሁሉ ፡ እየተናገረ
ይሄ ፡ አንደበቴ ፡ አንተን ፡ አስመረረ

በአንደበቴ ፡ ላክብርህ
ደስ ፡ የሚልህን ፡ ልናገርልህ (፪x)

ያምራል ፡ ስባል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ ብዬ
ትናንትናን ፡ ንቄው ፡ ዘግቼው ፡ አልፌ
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ምን ፡ ተገኝቶ
የናቁትን ፡ ማየት ፡ ኋላ ፡ ተመልሶ

በአደባባይ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ላመልክህ
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ሆኜ ፡ በፊትህ
ያልሆንኩትን ፡ ሆኜ ፡ በሰው ፡ ፊት ፡ ስታይ
መጥፊያዬ ፡ እንዳይሆን ፡ የምልህ ፡ አለኝ

በጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ ላክብርህ
ሰው ፡ ያላየው ፡ ባህሪዬ ፡ ያስደስትህ
በጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ ላክብርህ
ድብቅ ፡ ገመናዬ ፡ ያስደስትህ

እኔ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መሸነፍ ፡ በቃኝ
እኔ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መታለል ፡ በቃኝ
አዎ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መታለል ፡ በቃኝ
አዎ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መሸነፍ ፡ በቃኝ

በቃ ፡ በል ፡ እስቲ ፡ ጣልቃ ፡ ግባና
ሁሉ ፡ የሚያምረው ፡ በአንተ ፡ ነውና
በቃሽ ፡ በለኝ ፡ ጣልቃ ፡ ግባና
ሁሉ ፡ የሚሳካው ፡ በአንተ ፡ ነውና