ላሰናዳው ፡ ቤቴን (Lasenadaw Bietien) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

ይመጣል ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ይመጣል

በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ ተገልጦ ፡ መልአኩ
አዋጅ ፡ ነገራቸው ፡ ለእረኞች ፡ ሁሉ
ንጉሥ ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም ፡ ከተማ
ሄዳችሁ ፡ ስገዱ ፡ በግርግም ፡ አለና (፪x)

መላዕክት ፡ ያወጁለት ፡ እረኞች ፡ የሰገዱለት

አዝ፦ ይሄ ፡ ወዳጄ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል
እንዳልቀር ፡ ከደጅ ፡ ላሰናዳው ፡ ቤቴን (፪x)

ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ንፁህ ፡ ላድረገው ፡ ሕይወቴን (፪x)

ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ኢየሱስ ፡ ይመጣል
ኢየሱስ ፡ ይመጣል

በቃላ ፡ ገሊላ ፡ ጀመረ ፡ ተዓምሩ
የአባቱን ፡ ፈቃድ ፡ ፈፀመ ፡ ትዕዛዙን
ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ኃጢአት ፡ በመስቀል ፡ የሞተው
ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳው

አዝ፦ ይሄ ፡ ወዳጄ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል
እንዳልቀር ፡ ከደጅ ፡ ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ንፁህ ፡ ላድረገው ፡ ሕይወቴን (፪x)

እኔስ ፡ ልሁን ፡ ከልባሞቹ
መቅረዜን ፡ ልሙላ ፡ አላንቀላፋ
ድንገት ፡ ሲመጣ ፡ ይኼ ፡ ወዳጄ
እንዳልቀር ፡ ኋላ ፡ ካሁኑ ፡ ልንቃ

አዝ፦ ይሄ ፡ ወዳጄ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል
እንዳልቀር ፡ ከደጅ ፡ ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ላሰናዳው ፡ ቤቴን
ንፁህ ፡ ላድረገው ፡ ሕይወቴን (፪x)

የምድሩ ፡ ክብር ፡ ዝናው
ሲደምቅልኝ ፡ አቤት ፡ ጭብጨባው
ሞቅ ፡ ብሎ ፡ እንዳልዘነጋ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ሙግትሽህ ፡ ምንድን ፡ ነው
አይግረምሽ ፡ አይድነቅሽ
መዝገብም ፡ አይሆን ፡ ለላይኛው ፡ ቤቴ

ተይ ፡ ተይኝ ፡ ነፍሴ ፡ ተይኝ
ከአምላክሽ ፡ ጋራ ፡ ተስማሚልኝ
የሚረባን ፡ የሚያውቅ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ዎይ
የሚበጅሽንስ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ዎይ
በቃ ፡ ተይኛ ፡ ነፍሴ ፡ ተይኝ
ከአምላክሽ ፡ ጋራ ፡ ተስማሚልኝ