ላመስግንህ (Lamesgeneh) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

ላመሰግንህ ፡ ይገባኛል
ዝምታ ፡ ከእኔ ፡ ሊርቅ ፡ ግድ ፡ ይለኛል
ውለታ ፡ ያለበት ፡ ሰው
መስዋዕቱ ፡ ሁሌ ፡ ምሥጋና ፡ ነው

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ላመስግንህ ፡ በፊትህ ፡ ወድቄ
ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ላመስግንህ ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህን

ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

ተነሺ ፡ ዘምሪ ፡ ተቀኚ ፡ ለክብሩ
ይለኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ የበዛ ፡ ምህረቱ
የሳቅ ፡ ሆኖልኛል ፡ የደስታ ፡ ነው ፡ ቤቴ
እፎይታ ፡ ሆኖልኝ ፡ በኢየሱስ ፡ አባቴ

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ላመስግንህ ፡ በፊትህ ፡ ወድቄ
ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ላመስግንህ ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህን

ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ
ልዘምርልህ ፡ ላመስግንህ

ሞኝነት ፡ አይደለም ፡ ለእርሱ ፡ መዘመሬ
ነፍሱን ፡ ሰጥቶኝ ፡ ነው ፡ በሕይወት ፡ መኖሬ
ታዲያ ፡ ላመስግነው ፡ የምን ፡ ዝምታ ፡ ነው
ለወደደኝ ፡ ጌታ ፡ የፍቅር ፡ ቅኔ ፡ ነው

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ላመስግንህ ፡ በፊትህ ፡ ወድቄ
ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ላመስግንህ ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህን (፪x)