ህልውናህ (Helewenah) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

ህልውናህ ፡ ይውረሰው ፡ ሕይወቴን
መንፈስህ ፡ ይቃኘው ፡ ማንነቴን
ታማኝ ፡ ባሪያህ ፡ ሆኜ ፡ ላገልግል
ከመረጥከኝ ፡ ወደህ ፡ ልዘምርልህ (፪x)

አትሂድብኝ ፡ ከእኔ (፪x)
መኖር ፡ አልችልም ፡ ለብቻዬ (፪x)

ለብቻዬ ፡ አልፈልግም ፡ ለብቻዬ (፫x)
ለብቻዬ ፡ አልፈልግም ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ

ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ቢያይልም
ስታግዘኝ ፡ እንጂ ፡ መሄድህ
ነው ፡ . (1) . ፡ አልወድም
በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ
ኃጢአትን ፡ ነው ፡ እንጂ
ኃጢአተኛን ፡ አትጠላም ፡ አውቃለሁ

ያለ ፡ አንተማ ፡ መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ (፬x)

ህልውናህ ፡ ይውረሰው ፡ ሕይወቴን
መንፈስህ ፡ ይቃኘው ፡ ማንነቴን
ታማኝ ፡ ባሪያህ ፡ ሆኜ ፡ ላገልግል
ከመረጥከኝ ፡ ወደህ ፡ ልዘምርልህ (፪x)

አትሂድብኝ ፡ ከእኔ (፪x)
መኖር ፡ አልችልም ፡ ለብቻዬ (፪x)

ለብቻዬ ፡ አልፈልግም ፡ ለብቻዬ (፫x)
ለብቻዬ ፡ አልፈልግም ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ

ዝም ፡ ካልክ ፡ ፈራለሁ ፡ ድምፅህን ፡ ካልሰማው
ህልውናህ ፡ ከሌለ ፡ እንደ ፡ ሞተ ፡ ሰው ፡ ሆናለሁ
ጭር ፡ ሲል ፡ እፈራለሁ ፡ ድምፅህን ፡ ካልሰማው
ህልውናህ ፡ ከሌለ ፡ እንደ ፡ ሞተ ፡ ሰው ፡ ሆናለሁ

እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም
ከሩቁ ፡ ከደጅ ፡ መሆን ፡ አያምርብኝም (፪x)