ፈቃድህ (Feqadeh) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

የሕይወት ፡ መገኛ ፡ የዘለዓለም ፡ ውረት
ፈቃድህን ፡ ማድረግ ፡ ለሀሳብህ ፡ መወገድ
ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ አስቀድመህ ፡ ያኔ
የልጅህን ፡ መልክ ፡ እንድንሰው ፡ ነው ፡ ውሳኔ

ከታናሽነቴ ፡ ከብላቴንነት
የመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር
የለየኸኝ ፡ ጌታ ፡ በጐና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ
ፍፁም ፡ የሆነው

ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ ዘንድ ፡ በሕይወቴ
ጣልቃ ፡ ግባ ፡ በእያንዳንዱ ፡ ነገሬ
የሚረባኝ ፡ የሚበጀኝን
ታውቅልኝ ፡ አይደል ፡ አባቴ (፪x)

ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ በሕይወቴ (፫x)
አላማህ ፡ ይፈፀም ፡ በሕይወቴ (፫x)

ለእኔ ፡ ብዬ ፡ የምተወው ፡ (የምተወው)
አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ የምሸሽገው
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ (ሰጥቻለሁ)
ፈቃድህ ፡ እንዲፈፀም ፡ እወዳለሁ

ችላለሁ ፡ ብዬ ፡ የምተወው
አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ የምሸሽገው
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ (ሁሉን ፡ ለአንተ) ፡ ሰጥቻለሁ
ፈቃድህ ፡ እንዲፈፀም ፡ እወዳለሁ

የአንተ ፡ ሀሳብ
የአንተ ፡ አላማ
የአንተው ፡ ፈቃድ
በዘመኔ ፡ ይፈፀም (፪x)