እኔን ፡ ለክብር (Enien Lekeber) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

እኔን ፡ ለክብር ፡ ለሽልማት ፡ ያበቃኝ
እግዚአብሔር ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ አነሳኝ (፪x)
በሰው ፡ ዓይንም ፡ አልሞላ
ነኝ ፡ እኮ ፡ ደካማ
ግን ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ፡ የተወደድኩኝ
በእግዚአብሔር ፡ የተመረጥኩኝ (፪x)

ከሰው ፡ ተራ ፡ የሚያድን ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ የለኝ
ጐሽ ፡ የእኔ ፡ ልጅ ፡ ተብሎ ፡ የሚያስመሰግን
ምህረትህና ፡ ፍቅርህ ፡ ሰው ፡ አድርገውኛል
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ያዘምሩኛል

አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x)

እርቃንህን ፡ አደባባይ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ
ምንም ፡ ሳታጠፋ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተገፋህ
ያ ፡ ሁሉ ፡ ልፋትህ ፡ እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው
ከክብርህ ፡ ወርደህ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያልከው

አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x)

እኔን ፡ ለክብር ፡ ለሽልማት ፡ ያበቃኝ
እግዚአብሔር ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ አነሳኝ (፪x)
በሰው ፡ ዓይንም ፡ አልሞላ
ነኝ ፡ እኮ ፡ ደካማ
ግን ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ፡ የተወደድኩኝ
በእግዚአብሔር ፡ የተመረጥኩኝ (፪x)

ሰው ፡ ሰውን ፡ የሚወደው ፡ በእራሱ ፡ ምርጫ ፡ ነው
ድካም ፡ ያለበትን ፡ ማነው ፡ የሚቀበለው
አንተ ፡ ግን ፡ ስትወደኝ ፡ ስትቀበለኝ
ደካማ ፡ ነሽ ፡ ብለህ ፡ ፊትህን ፡ አልነሳኸኝ

አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x)