እንደገና (Endegena) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ
እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ
እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x)

እንደ ፡ ኃጢአት ፡ ብዛት ፡ አልፈረከብኝ
እግዚአብሔር ፡ ምህረቱን ፡ አልከለከለኝ
በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ምህረት ፡ ባልኩበት
ይቅርታ ፡ በዝቶልኝ ፡ ይኸው ፡ ዘመርኩለት

አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ
እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ
እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x)

ሊከሱኝ ፡ ወደው ፡ ኃጢአተኛ ፡ ብለው
በድንጋይ ፡ ሊወግሩኝ ፡ ዳኛ ፡ ፊት ፡ አቅርበው
የተገባኝን ፡ ሞት ፡ አይገባም ፡ ብሎ
ምህረት ፡ አረገልኝ ፡ ሀፍረቴን ፡ ከልክሎ

አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ
እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ
እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x)

የምህረት ፡ አምላክ ፡ ደጁ ፡ ተከፈተ
ለብዙ ፡ በደሌ ፡ ይቅርታ ፡ . (1) .
እንደገና ፡ ቆሜ ፡ ፊቱ ፡ ዘምራለሁ
የማረኝን ፡ አምላክ ፡ አመሰግናለሁ

አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ
እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ
እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x)