From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አርነት ፡ ከበደ (Arenet Kebede)
|
|
፩ (1)
|
ለምን (Lemen)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፭ (2012)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፪ (12)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:53
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች (Albums by Arenet Kebede)
|
|
አዝ፦ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ
የልቤን ፡ ተረድቶ ፡ እንባ ፡ የሚያብስ ፡ ከዓይኔ (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)
ትናንትና ፡ እንዴት ፡ ይታለፍ
ጭንቅ ፡ ነበር ፡ ለብቻ ፡ ሲታሰብ
በዙሪያዬ ፡ ጠላት ፡ ከቦኝ
ማን ፡ ያድነኝ ፡ ብዬ ፡ ተረበሽኩኝ
ሰማያት ፡ ተከፈቱና
በተከበበው ፡ ከተማ
ምህረቱን ፡ አበዛልኛ (፪x)
ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነህ (፮x)
አዝ፦ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ
የልቤን ፡ ተረድቶ ፡ እንባ ፡ የሚያብስ ፡ ከዓይኔ (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)
ስደክምበት ፡ ዞር ፡ በይ ፡ ደካማ
አላለኝ ፡ ደግ ፡ ነው ፡ ጌታ
አቅም ፡ ሆነ ፡ ኃይል ፡ አስታጠቀኝ
በከፍታ ፡ ላይ ፡ አቆመኝ
ሰማያት ፡ ተከፈቱና
በተከበበው ፡ ከተማ
ምህረቱን ፡ አበዛልኛ (፪x)
ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነህ (፮x)
|