እግዚአብሔር ፡ ሲናገር (Egziabhier Sinager) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

የሚገርመኝ ፡ እኔ ፡ ቅጥሩ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ማንም ፡ እንዳይነካኝ ፡ ለእኔ ፡ ያሰበው
ተዘልለሽ ፡ ኑሪ ፡ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ
ለምን ፡ ትፈሪያለሽ ፡ . (1) .

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር
ሰማሁ ፡ ተነሳሁ
እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ
ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x)

እኔን ፡ የሚጠብቅ ፡ አይተኛ ፡ አያንቀላፋ
ይልቁን ፡ በእሳቱ ፡ ጠላቴን ፡ አጠፋ
ክንዱ ፡ ተዘርግታ ፡ አርፌ ፡ በጌታ
ሳልሰጋ ፡ ኖራለሁ ፡ ሁልጊዜም ፡ በደስታ

እርግማን ፡ እንዳይሰራ ፡ በዘመኔ
ሟርትም ፡ እንዳይሰራ ፡ በዘመኔ
ቅጥር ፡ ሆንከኝ ፡ መድህኔ (፫x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር
ሰማሁ ፡ ተነሳሁ
እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ
ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x)

የጠላቴን ፡ ምክር ፡ ዛቻውን ፡ እንዳልፈራ
በእሳት ፡ የሚመልስ ፡ አለኝ ፡ የሚያኮራ
ዙሪያዬ ፡ ቢዞር ፡ ጠላት ፡ ቢጮህ
መናወጥ ፡ አላውቅ ፡ ሰላሜ ፡ አይጠፋ

እግዚአብሔር ፡ ብሎኛል ፡ ልጄ ፡ እረፊ
በዘመንሽ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ለአንቺ
ሰላም ፡ ይሁን ፡ ከቤትሽ (፫x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር
ሰማሁ ፡ ተነሳሁ
እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ
ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x)