በኃይሌ ፡ እንዳልል (Behaylie Endalel) - አርነት ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አርነት ፡ ከበደ
(Arenet Kebede)

Arenet Kebede 1.jpg


(1)

ለምን
(Lemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአርነት ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Arenet Kebede)

አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ
አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት (፪x)

ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለም
ለመዳኔ ፡ ምክኒያት ፡ ምንም ፡ አልፈጠርኩ
ታሪኬ ፡ እንዲያምር ፡ ከክብሩ ፡ ወረደ
ሕይወቱን ፡ ሊሰጠን ፡ እራሱን ፡ አዋረደ
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x)

አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ
አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት

ሰራሁት ፡ የምለው ፡ አከናወንኩት
ዛሬ ፡ ለመድረሴ ፡ እኔስ ፡ ለፋሁበት
የምለው ፡ የለኝ ፡ ድካሜ ፡ ነው ፡ ቀላ
ግን ፡ በእርሱ ፡ ምህረት ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x)

አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ
አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት

እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው ፡ ስቃዩ ፡ የበዛው
የደም ፡ ላብ ፡ ያላበው ፡ በመስቀል ፡ የሞተው
ሞቴን ፡ የሞተልኝ ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል
የዘለዓለም ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ አድርጐኛል
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x)