ክብሬ ፡ ነህ (Kebrie Neh) - አናን ፡ ደሳለኝ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አናን ፡ ደሳለኝ
(Anan Dessalegn)

Anan Dessalegn 2.jpg


(2)

እንካ ዘላላሜን
(እንካ ዘላለሜን)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአናን ፡ ደሳለኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Anan Dessalegn)

ክብሬ ነህ

1- የጠላቴን ሳቅ ልትገታ
ከኔ ቤት ገባህ ጌታ
ከብዙ በሚሻል ፍሬ
ሳሙኤልን አወጣህ ከኔ
       ታምነውህ እንደማታሳፍር
       ውርደቴን ለውጠህ በክብር
       አሳየህ ውድ ወዳጅነትህን
       ዘንበል እንድትል ሚጠና ደጅህን

አዝ፡ ላመስግንህ፤ ላመስግንህ
ክብሬ ኢየሱስ አንተ ነህ

2- ቢመስልም የወይን ጠጅ ውጤት
መጮኼ ማንባቴ ቀን ከሌት
አንደበት አልፈህ ልብ የምታይ
አንተ ግን አደመጥከኝ ከላይ
      ዘንበል አልክ ከዙፋንህ
      አጠጣኸኝ ከመንፈስህ
      መፅናናት አይደል ሽረት ነው
      ለሀዘን ጭንቀቴ የሆነው
የማንም እንባ ባለእዳ አይደለህም
ንግግሬ ባንተ ዘንድ እንደቀልድ አይታይም
ትወርድልኛለህ ሰማይን ዝቅ አድርገህ
ያለቀስኩበትን/የቆዘምኩበትን ዘመኔን ልትክስ አስቀህ

 አዝ፡ ላመስግንህ፤ ላመስግንህ
     ክብሬ ኢየሱስ አንተ ነህ