From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ለፍቻለሁ
በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ እሮጫለሁ (፪x)
ያላንተማ ፡ ደስ ፡ ብሎት ፡ ተድላን ፡ የቀመሰ ፡ እንደሌለ
በጐ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት ፡ ከላይ ፡ እንደሆነ (፪x)
የገባኝ ፡ ያው ፡ ብዙ ፡ ለፍቻለሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በቃ ፡ አቅም ፡ አጥቻለሁ
ያስጨነቀኝ ፡ የረበሸኝ ፡ የዛሬውን ፡ ነገሬ
ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ዘመኔን
እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (እንካ)
እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (፪x)
እንካ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ዘል-ዘለዓለሜን (ዘላለሜን)
ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ኑሮዬን
በቃ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ዘል-ዘለዓለሜን (በቃ)
ጌታ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘመኔን
በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ለፍቻለሁ
በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ እሮጫለሁ (፪x)
በከንቱ ፡ ይደክማል ፡ ቤተ ፡ ሰሪ
በከንቱ ፡ ቅጥር ፡ ጠባቂ
በሌለህበት ፡ ከንቱ ፡ ሩጫ
መውደቅ ፡ መላላጥ ፡ መታመም ፡ ብቻ (፪x)
የገባኝ ፡ ያው ፡ ብዙ ፡ ለፍቻለሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በቃ ፡ አቅም ፡ አጥቻለሁ
ያስጨነቀኝ ፡ የረበሸኝ ፡ የዛሬውን ፡ ነገሬ
ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ዘመኔን
እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (፬x)
እንካ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘለዓለሜን
ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘመኔን
በቃ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ እንካ ፡ ዘላለሜን (በቃ)
ጌታ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ውሰድ ፡ ዘመኔን
|