የእንጨትነት ፡ ሕይወት (Yenchetinet Hiwot) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

ልፋ ያለው እንጨት - እድሉ የጠመመ
ባሬላ ተብሎ - እየተሰየመ
ያንን ኩንታል ድንጋይ - እየተሸከመ
-
ደግሞ ሌላው እንጨት - የ'ንጨት እድላሙ
መስቀል ነህ ተብሎ - ተሰይሞ ስሙ
አላፊ፣ አግዳሚ - እ'ሱን እንዲያስሙ
ቀሳውስትን ቀጥሮ - በተቀባ ስሙ

አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ
ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x


የተቀባው እንጨት - ካ'ናት ይሰቀላል
ሌላ ታናሽ ረግጦ - በእንጨት መሰላል
ካ'ናት ጋር እስኪደር - አንዱ ባ'ንዱ ልቆ
በእንጨት ገበያ - እንጨት በ'ንጨት ደምቆ

አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ
ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x


ቢያቃጥሉት አመድ - ቢቆርጡትም ጉቶ
ቢለበለብ ከሰል - ጉቶነቱን ትቶ
ለያይተነው እንጂ - ስሙን ሸልመነው
ከንቱ ተሰባሪ - እንጨት ያው እንጨት ነው

አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ
ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x


ምንም አንዱ ቢገን - ሌላው መሬት ቢልስ
መፈራት ያለበት - የ'ንጭቶቹ ጌታ - በ'ሳት የሚመልስ 2x