From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እንዳላየ በሚያልፍበት - የከበበኝ ይህ ሁሉ ሰው
በሞት ጥላ ስር ካለሁበት - እግዚአብሔር ነው የደረሰው! [አዝ]
“በችግሩ - ‘እግዚአብሔር ሆይ’ - ለምን ይላል - በደረቁ”
“አላየዉም - አልሰማዉም” - ብለው ሳቁ ተሳለቁ!
አምላኬ ግን - አልሰጠኝም - ለሳቁብኝ አሳልፎ
ድካሞቼን - አስወገደ - እንደጊዜው አረጋግፎ!
[አዝ]
ብዙ ሰልፎች - በነፍሴ ላይ - ሲንጓደዱ እየዋሉ
አልፎኝ ሄዷል ብዙ ጊዜ - ከንፈር መጦ ሰው ላመሉ!
“ማን ያድነኝ?” ባልኩት ጩኸት - ይነግዳል ግብዝ መንጋ
በዙሪያዬ ካሉ እጆች - የ’ሱ ብቻ ተዘረጋ!
[አዝ]
ትናንትና በደም ገንዝብ - ኑሮ አቁመው የደመቁ
አሁን የሉም ጠፋፍተዋል - እንደጤዛ አየደረቁ!
ለምለም መሳይ የጊዜያዊ - መንገዶችን በለመዱ
ዛሬ አልቀናም ተምሬያለሁ - እሄዳለሁ በመንገዱ!
[አዝ]
የሰው ልቡ ይታበያል - መነሻዉን እየረሳ
ቀን ሲያልፍለት እድል ሲያገኝ - የወደቀን አያነሳ!
በመከራ መሸሸጊያ - በክፉ ቀን የሚጠራ
እግዚአብሔር ነው ፈጥኖ ደራሽ - እንደጊዜው የሚሰራ!
[አዝ]
|