From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አመፀኞችን አየሁና - ከተመኙት በላይ ሲያገኙ
ሀብት ስኬታቸው በዝቶ - ሰርክ በደስታ ሲዋኙ
እጆቼን ማጠብ ማንፃቴ - ልቤንም ማቅናት ማፅደቄ
በከንቱ መስሎ ቢሰማኝ - በራሴው አይኖች ተንቄ
ለመውደቅ ትንሽ ሲቀረኝ - ሊሰናከሉ እግሮቼ
ከሰው ጋር ባልተገረፉ - በሀጥዓን ሰላም ቀንቼ
አምላኬ አንተን አሰብኩኝ - በማየው እየተፈተንኩ
ግና መቅደስህ ገብቼ - ፍፃሜኣቸውን አስተዋልኩ!
ዘውትር ቀኝ እጄን የያዝከኝ - ያደረግከኝ ከአንተ ጋር
ሁሌም በምክርህ መርተኸኝ - የተቀበልከኝ በክብር
ሥራና ሀሳብህን ስቼ - በማየው ነገር ጎድዬ
የልጆችህን ትውልድ - እንዳልኖር በኣፌ በድዬ
በማስተዋልህ ጠብቀኝ - በቤትህ ይለቅ ዕድሜዬ [አዝ]
ከ'ሪያ ጋር ኖሮ ሲያበቃ - ወዳንተ ለመጣ ከስሮ
ምህረትህን ማታርቅ - የማትመልስ ፊትህ ጠቁሮ
አያውቅም ባሉህ ግፈኞች - በትዕቢተኞች ስቀና
ወደ መቅደስህ መለስከኝ - ማስተዋል ሰጠኸኝና
የኖራ ልስን መቃብር - ነበረ ለካ ስኬቴ
በድጥ ላይ የተቀመጠ - ከጸጋህ 'ሚያጎል ከቤቴ
[አዝ]
በላይ በሰማይ ምን አለኝ በጠፈር?
የልቤ አምላክ ሆይ - ካንተ በቀር
ታችስ በምድር ምን አለኝ ምን ነገር?
የልቤ አምላክ ሆይ - ካንተ በቀር
[አዝ]
እድል ስታበዛላቸው (ስለፀኑ በሃጢአታቸው)
ወዳንተ መቅረብ የጠሉ (ስለፀኑ በሃጢአታቸው)
በቀረብካቸው መጠን (ስለፀኑ በሃጢአታቸው)
ካንተ ሚርቁ ይጠፋሉ (ስለፀኑ በሃጢአታቸው)
እግዚአብሔር ነህ መታመኛ (እየዘመርኩ በምስጋና)
የዘላለም ዕድል ፈንታ (እየዘመርኩ በምስጋና)
ይለቅ በቤትህ ዘመኔ (እየዘመርኩ በምስጋና)
ህይወቴ ላይ ግነን ጌታ (እየዘመርኩ በምስጋና)
|