From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አምላኬ ንጉሥ ሆይ፥ ከፍ አደርግሃለሁ፥
(አመሰግናለሁ) 2x
ስምህንም ለዘላለም እባርካለሁ።
(አመሰግናለሁ) 2x
ክበር እንጂ ተመስገን እንጂ
ሌላ ምን ቃላት አለኝ ላንት ለወዳጄ
ንገሥ እንጂ ከፍ በል እንጂ
ሌላ ምን ቃላት አለኝ ላንት ለወዳጄ
ከትውልድ ትውልደ ሥራህን - ያመሰግናሉ፥
የቅድስናህን ግርማ - ክብርህን ይናገራሉ፥
ታላቅነትህን አስታውሰው - ብርታትህን ያውጃሉ።
በቸርነትህ ብዛት - በጽድቅህ ሐሤት ያደርጋሉ።
[አዝ]
አቤቱ፥ የ'ጅ ሥራው ሁሉ - ሚያመሰግኑት ይሄ ጌታ፥
ኃይልህን የሚያስታጥቅ በሰልፍም - እጅጉን የበረታ
ከቍጣ ፈፀሞ የራቀ - ምሕረቱ እጅጉን የበዛ
ለመጣው እጁን ከፋች - ነፍሱ በተስፋ ተይዛ
[አዝ]
ለሚታገሡት ቸር አምላክ - ከፍጥረት ሁሉ የላቀ
በሥራውም ሁሌ ጻድቅ - በመንገዱ የታወቀ
መልካሙንም አጥጋቢ - ምሕረቱ የገነነ
ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ - ለመስማትም ቅርብ የሆነ
[አዝ]
አፌ የአንተን ምስጋና ይናገራል፤
ፍጥረት ሁሉ ስምህን ሁልጊዜ ያወራል።
በእውነትም እግዚአብሔር ታላቅ ነህ
ለታላቅነትህም ፍጻሜ የሌለህ።
|