ምስክር ነን እኛ! (Misikir Nen Egna!) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

በተጣለች አለም - መሃል የዘመትን
የምንለመልም - ዘዉትር እየሞትን
ትውልድን ለማትረፍ - ከዘላለም ቁጣ
የመዳንን ወንጌል - ይዘን የምንወጣ…
(ምስክር ነን እኛ!) - [አዝ]


ጥበባችን ሁሉ - ሞኝነት ‘ሚመስል
የእግ’ዚአብሔርን ፍቅር - ለሰው የምንስል
ሲረግሙን መራቂ - ላሳዳጆች ፀላይ
መልካም የምንመኝ - ጠላቶቻችን ላይ…
ምስክር ነን እኛ!

[አዝ]


ዋጋችን በሰማይ - ሀይላችን በፀሎት
ምንዳን የማንሻ - ለምድር አገልግሎት
ኢየሱስን ይዘን - የማናቀረቅር
መንገዳችን ቀና - እርምጃችን ፍቅር…
ምስክር ነን እኛ!

[አዝ]


“የምን ደርሶ አዋቂ - የምን ደርሶ አቡን
አጉል ጠበቃዎች…” - ሲሉ ቢያዋክቡን
ቢያላጉን በጥፊ - ቢያዳፉን በጡጫ
በስል ምላሳቸው - ብንሆን ማላገጫ…
ምስክር ነን እኛ!

[አዝ]


በሞት ጥላ ግርዶሽ - ተከበው ለኖሩ
ብቃት አጣን ብለው - አጋዥ ለሚጠሩ
የምስራች ይዘን - ለህዝቡ ወጥተናል
ዛሬም እንላለን - ኢየሱስ ያድናል!!
(ኢየሱስ ያድናል)