ልወቅህ (Leweqeh) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

ላንተ ክብርን ሳቀርብ - ስሰዋ ምስጋና
በልኬ ሰፍቼ እንዳላሳንስህ - እፈራለሁና
ደስ በሚያሰኝህ - አይነት እንዳመልክህ
አንተን አስተምረኝ - እንዳውቅህ በልክህ

ልወቅህ ጌታዬ - ደስ ተሰኝብኝ
በቃየን መሰዊያ - መስዋዕቴ አይገኝ - [አዝ]


ነፍሴ ሀሴት አድርጋ - ዝማሬ ‘ሰማለሁ
ከሚያመልኩህ ጋራ - አብሬ አምልኬአለሁ
“አባት አልልህም” - ሲሉህ አጅቤኣለሁ
ግን ካንተ ወዲያ አባት - ከየት አገኛለሁ?

[አዝ]

ልወቅህ ጌታዬ - ልሁን ባንተ ቅጥር
ባንተ ድልን ሳገኝ - ጦሬን እንዳልቆጥር - 2x


ላንተ የማቀርበው - ንጹህ መስዋዕቴ
ምሉዕ እንዲሆንልኝ - ቢሳካ ምኞቴ
ልቦናዬን አብራው - ክብርህን እንዳየው
ከስጦታ በላይ - ሰጪውን ልለየው!

[አዝ]

ትወቅህ ይኽች ልቤ - በቃልህ አሙቃት
እንዳሻት እንዳትሆን - ከጥፋት ጠብቃት - 2x

ሁሌ እንደለመድኩት - ስላደረግከው ድንቅ
ወይም ድል ለማግኘት - ስለከበበኝ ጭንቅ
አይሁን ጌታዬ ሆይ - ስብከቴን ጨምቄ
ላምልክ እንጂ ገብቶኝ - ክብርህን አውቄ