ገናና (Genana) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

አቤቱ በስራህ - ስምህ የገነነ
በሰማይ በምድር - የተመሰገነ፤
ያንተን ህልውና - የሚጠራጠሩ
በእጆችህ ስራ - ከምክንያት አጠሩ።

ገናና ነህ ዝነኛ
የፍጥረት ምንጩ መገኛ
ጅማሬህን አናውቀው - ፍፃሜህን አናውቀው
በ'ድሜያችን በምናውቅህ - ስራህን እናድንቀው!


ጥበብህ ሰላምህ - ላ'ለም የሚበቃ
ድንቅ፥ መካር፥ ኃያል - የሰላም አለቃ፤
መላእክት ባንድ ላይ - ቅዱስ ነህ ይሉሃል
የለም የሚመስልህ - ከሚኖሩት መሃል።

[አዝ]


ባ'ንተ ያለን ሞኝነት - ከእውቀት ሚዛን ቢጣል
ባ'ለም ካሉ ጥበቦች - ብዙ ርቀት ይበልጣል፤
ያ'ንተ ስራ ሲታወጅ - በምድር ላለ አካል
ምስጋናህ በህዝብህ ላይ - እንዳ'በባ ይፈካል።

[አዝ]


ስ'ሰጠን ተመስገን፥ ስታስቀር ተመስገን
ያልነውን ነው እንጂ - ያልከውን አትነፍገን፤
ከምናውቅህ በላይ - ስምህ ከፍ ያለ ነው
አፍረንብት አናውቅም - አንድ ጊዜም ጠርተነው።


በክብርህ የመጡን - እግዚአብሔር ተዋጊ
ከቤትህ የጠፉን - እግዚአብሔር ፈላጊ፤
እግዚአብሔር ኃይለኛ - እግዚአብሔር ከፍታ
እግዚአብሔር አምባችን - እግዚአብሔር መከታ!

እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር

እግዚአብሔር አንተን ነው - ዘውትር የምንጠራው
የትኛው ጀግና ነው - አንተን የሚያስፈራው!