አትመጣም ወዪ? (Atimetam Wey?) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 7:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

አትመጣም ወዪ - ኧረ አትመጣም ወዪ
ዛሬም አሻቅበናል - ወደሰማዪ
አትመጣም ወዪ - ዉዴ መምጫህ ናፈቀን
የከለለህ ደመና - መልክህን ደበቀን!

ጥንት የተሰራው ስራ - ዛሬ የሆነ መስሎ
በፊታችን ትይዩ - መሰቀልህ ተስሎ
አንተን አንተን እያልን - ዛሬም እዛ’ው ቆመናል
ልክ እንደሄድከው ሁሉ - ብትመጣልን ምናል?

[አዝ]


ዳግም መምጫህ ናፍቆናል - የፍጥረትህ ማረፊያ
ነፃ የምንወጣበት - ከአለም ትግል ልፊያ
እመጣለሁ እንዳልከን - እንደቃልህ ድንገት ና
በመምጣትህ ገላግለን - ካ’ለማዊ ፈተና!

[አዝ]


የስጋ ኑሮ ታከተን - የእድሜ ሙሉ ድካም
በምናገኘው ሁሉ - ልባችን ከቶ አይረካም
ትናንት ቆመናል ባልነው - ዛሬ ጠልፎን ወድቀናል
ኢየሱስ ቶሎ ናልን - ሁሉ መልካም ይሆናል!

[አዝ]


የኛን ጉጉት የሚያዩ - ጌታ በዚህ ነው ቢሉን
የመምጫህ ቁርጡን ጊዜ - አንድም ባናውቀው ውሉን
በከንቱ ጓዳ ሳይሆን - ዙሪያህ ሆኖ ደመና
አለምን ያናውጣል - የመመለስህ ዝና!

[አዝ]