From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
ያልተቀበልነው - ምን ምን አለ?
ሁሉ በርሱ ነው - ሞላ፥ ጎደለ
ለገባው ቃሉ - የታመነ
እግዚአብሔር ነው - የገነነ
እግዚአብሔር ብቻ ነው - የመስጠት ልኩ
ተቀብላችሁ - ክብሩን አትንኩ
ቢጎል ቢሞላ - ለነፍስ ዋስትና
ሲጠማን ምንጭ ነው - ሲርበን መና! - [አዝ]
ደከመኝ አይል - አጋዥ አይሻ
በራሱ ሙሉ - የራሱ ጋሻ
ታክቶት አላየን - እንደዛለ ሰው
አንዴም አልሰማን - ጉልበቱ ሲያንሰው!
[አዝ]
ይኼ ማን ነው - ባህር ያቆመ
የህዝቡን ማዳን - የፈፀመ?
ኧረ ይህ ማን ነው - የማዕዘን አለት
ፍጥረታት ሁሉ - የሚገዙለት?
በ'ፍኙ የሚሰፍር - ያሉትን ቀላያት
በምድርም ያሉ - የሰማይም ሰማያት፤
በኃይል የታሰሩትን - ፈቶ የለቀቀ
የሚጋፉን ዓለማት - ሰብስቦ ያረቀ!
ጫንቃችን ላይ በዝቶ - የኃጢያት እዳችን
በፍርድ ስር ሳለን - መውጫ መንገዳችን፤
የብርሃን መገኛ - የሰው ልብ ያበራ
የፍጥረት ፈጣሪ - ማዳኑን የሰራ!
እግዚአብሔር ብቻ ነው - የመስጠት ልኩ
ተቀብላችሁ - ክብሩን አትንኩ
ቢጎል ቢሞላ - ለነፍስ ዋስትና
ሲጠማን ምንጭ ነው - ሲርበን መና!
በ'ፍኙ የሚሰፍር - ያሉትን ቀላያት
በምድርም ያሉ - የሰማይም ሰማያት፤
የብርሃን መገኛ - የሰው ልብ ያበራ
የፍጥረት ፈጣሪ - ማዳኑን የሰራ!
ኢየሱስ ክርስቶስ - መድኅኒተ አለሙ
በፍጥረት ሁሉ ፊት - ገናና ነው ስሙ። 2x
|