አንተ ፡ ሰባኪ (Ante Sebaki) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

አንተ ሰባኪ ሆይ
ስማኝ አንተ ሰባኪ ሆይ

በያደባባዩ መዳንን - ላጣ ሰው
ለማይሞላ ሆዱ - ተስፋን ስታጎርሰው
አለምን መረጠ - ከኢየሱስ ስራ
በወንጌል መጫሚያ - ንዋይ ስትጠራ

አንተ ሰባኪ ሆይ
ስማኝ አንተ ሰባኪ ሆይ


አንድም ስንወድቅ ነው - አንድም ስንነሳ
የኢየሱስ ስራ - በኛ የሚወሳ
ትሾማለህ ብቻ - ትበላለህ ብቻ
ማዳኑን አትተካ - በገንዘብ እንጎቻ

[አዝ]


የጠበቀህ እንዲሁ - 'ካስፈሪ ማዕበል
ከልሎኝ ነቅ እንጂ - ሀይሌ ነው አትበል
በእኔነት ካባ - አለባብሰው ቢያርሱ
   (ኃላ ለአረም ነው)
የሚገልም እሱ - የሚያድንም እሱ

[አዝ]


አእላፋት በ'ጆችህ - ባ'ደራ ሲሰጡ
አንተን ሊከተሉ - ከየጫፍ ቢመጡ
ባውርቷ'ደር መሃል - ባ'ስመሳይ ጎዳና
በኑሮህም አፅና - የቃልህን ዳና

[አዝ]