አላውቅም (Alawkim) - አሉላ ፡ ጌታሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አሉላ ፡ ጌታሁን
(Alula Getahun)

Alula Getahun 1.jpg


(1)

አስይዘኝ ፡ መስቀሉን
(Asyizegn Meskelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 7:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሉላ ፡ ጌታሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Alula Getahun)

ከህግ በታች ያለን - በተጣለ ስጋ
እዳን የሚከፍል - የበቃን ፍለጋ
ማን ያድነን ብለን - ስንጠብቅ ተዓምር
ማህተሙን ፈቶ - በራሱ ሞት ‘ሚምር

አላውቅም - ከሰው በደል በላይ
አላውቅም - የሰው ድካም አሞት
አላውቅም - በፅድቅ ሆኖ ሳለ
አላውቅም - ለኃጥአን የሚሞት…

ለካ ግን አለ - ስሙ ማይከስም
ሞቶ የተነሳ - ሰማሁ አንድ ስም

[ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x


ለገዛ ፍርዳቸው - ምትክ ልሁን ባለ
ለሚሳለቁበት - መስቀል ላይ እንዳለ
ላደረጉት ሁሉ - ምህረት የሚለምን
አንዱን ብቻ ሰምተን - እንዲህ የተገረምን

አላውቅም - እንዲህ ያለ ነገር
አላውቅም - ድንቅ የሆነ ወሬ
አላውቅም - በጆሮዬ አልገባም
አላውቅም - ነበር እስከዛሬ….

ለካ ግን አለ - ባለይቅርታ
ሰማሁ አንድ ስም - እንዲ ያለ ጌታ….

[ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x


ድኩም መስሎ መምጣት - ታላቅ ክብሩን ትቶ
ክብርን ከጠገበ - አልጠብቅም ከቶ
እንዴት ያለ ንጉስ - እንዴት ያለ ኃያል
ሀይሉን በገዛ እጁ - ትቶ ፍዳን ያያል?

አላውቅም - በዙፋን ላይ ሳለ
አላውቅም - የደካማ ወዳጅ
አላውቅም - ክብሩን ትቶ ሚወርድ
አላውቅም - ያላንዳች አስገዳጅ....

ለካ ግን አለ - ለኛ የሚገደው
አንድ ስም አለ - ፍርዱን የናደው...

[ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x