ምሥጋናዬ (Mesganayie) - አሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን
(Ahava Gospo Singers)

Ahava Gospo Singers 1.jpg

(1)

Good Morning
(Good Morning)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Ahava Gospo Singers)

ሰው ፡ . (1) . ፡ ሳላንቀላፋ (ሳላንቀላፋ)
ጠላቴ ፡ እንደሳቀ ፡ ልቤ ፡ . (፪) .
በጊዜው ፡ ደርሰህ ፡ ሕይወቴን ፡ ቀጥለሃል
ከጠላቴ ፡ እጅ ፡ ነጻ ፡ አውጥተኸኛል

አዝ፦ ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አድርገህልኛልና ፡ አመልክሃለሁ
ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ

ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ስበሃል (እኔን ፡ ስበሃል)
ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ሳለሁ ፡ በኃጢአቴ ፡ እየጠፋሁ
በምህረትህ ፡ ልጅህ ፡ አድርገኸኛል
ታማኝ ፡ አድርገህ ፡ ለክብርህ ፡ አብቅተኸኛል

አዝ፦ ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አድርገህልኛልና ፡ አመልክሃለሁ
ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ

ስላደረክልኝ ፡ ምሥጋናን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ መጣሁ
እጆቼን ፡ ወደላይ ፡ ከፍ ፡ አድርጌ ፡ አነሳለሁ
ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ይሄው
አመሰግንሃለሁ

አዝ፦ ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ

ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አድርገህልኛልና ፡ አመልክሃለሁ (አምላክ ፡ ነህና)
ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ (በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ)
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ (አምላክ ፡ ነህና) (፪x)

አምላክ ፡ ነህና ፡ አምላክ (፬x)
አምላክ ፡ ነህና