ማራናታ (Maranatha) - አሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን
(Ahava Gospo Singers)

Ahava Gospo Singers 1.jpg


(1)

Good Morning
(Good Morning)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአሃቫ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Ahava Gospo Singers)

ዘመኑ ፡ አብቅቶ ፡ አልቆ ፡ ሰዓቱም ፡ ደርሷል
የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ መምጫ
በቶሎ ፡ መጣለሁ ፡ ልክ ፡ እንዳለው
እርሱ ፡ በደጅ ፡ ነው (፪x)

እንግዲህ ፡ የተዘጋጀው
ጌታውን ፡ ታምኖ ፡ የጠበቀው
ለእርሱ ፡ በቶሎ ፡ ይመጣል
ሽልማቱን ፡ ሊሰጠው

አዝ፦ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ (፬x)
አሜን ፡ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ና (፬x)

አዲስ ፡ ሰማይና ፡ አዲስ ፡ ምድር
እግዚአብሔር ፡ ለሕዝቡ ፡ ያዘጋጀው
ከነሱ ፡ ጋር ፡ አብሮ ፡ በአንድ ፡ ላይ ፡ ሊኖር
እርሱ ፡ በደጅ ፡ ነው

እንግዲህ ፡ የተዘጋጀው
እድፉንም ፡ በደሙ ፡ ያነጻው
እርሱ ፡ በዚያ ፡ ይኖራል
የንጉሡን ፡ ፊት ፡ እያየው

አዝ፦ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ (፬x)
አሜን ፡ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ና (፬x)

ና ፡ ይበል ፡ ጠቢብ ፡ የሆነ
ነፍሱን ፡ ከእሳት ፡ ሊያድን ፡ የወደደ
የሚያድነን ፡ አዳኝ ፡ ከአብ ፡ የተላከ
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ አይዞህ ፡ ጋብዘው ፡ ወዳንተ

አዝ፦ አሜን ፡ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ና (፬x)
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ (፬x)
አሜን ፡ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ና (፬x)
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ (፬x)
አሜን ፡ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ና (፪x)