ዘመኔን ፡ እንደ ፡ ቀድሞ ፡ አድስ (Zemenien Ende Kedmo Addis) - አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የድል ፡ ዘመን
(Yedil Zemen)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

ዘመኔን እንደቀድሞ አድስ
በመንፈስ ጀምሬ በስጋ እንዳልጨርስ
ዘመኔን እንደቀድሞ አድስ /4

መንፈሳዊነቴ ሰሞንኛ ሆኖ
ከትጋቴ ይልቅ መታከቴ ገኖ
የከበርኩበትን ሳዋርድ እንዳልገኝ
እስከሞት ልታመን ሃይልህን አልብሰኝ

ለቃል ለጸሎቱ መትጋቴ ቀረና
ስሸሽ እኖራለሁ ተብትቦኝ ስንፍና
ነውና ትእዛዝህ ህይወት የሚገኝበት
መመሪያዬ ይሁን ውዬ የማድርበት

የቀደመው ፍቅር ሆኖብኝ ትዝታ
በነበር እኖራለሁ የጥንቱን ሳወሳ
የሄደብኝ ምርኮ በእጥፍ ይመለስ
ድካም ያዳከመው ዳግም ይንቀሳቀስ

ከአንተ ጋር ያላከማቸ ይበትናል
ልፋቱን በቀዳዳ ኪስ ይጨምራል
አንተ ካለህ ይበዛልኛል ጥቂት ያልኩቱ
በማዳንህ በመተማመን የዘራሁቱ