በህልውናህ (Behelewenah) - አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የድል ፡ ዘመን
(Yedil Zemen)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

በህልውናህ /2/ በመገኘትህ /2/
የማይሆንልኝ ነገር የለም /2/
ሁሉ ነው ቀላል /2/ ላመስግንህ
ሁሉ ነው ቀላል /2/

በመገኝትህ ምስኪኖች ከአፈር ከታች ተነሱ
በመገኘትህ እየሳቁ ነው ብዙ ያለቀሱ
በመገኘትህ ሞታችው በሕይወት የተቀየረ
በመገኘትህ አንደበታቸው ለአንተ ዘመረ

የምፈልገው ሕልውናህን
ነፍሴ የምትሻው መገኘትህን /2/
ከዚያማ ሁሉ ነው ቀላል /4/

በህልውናህ /2/ በመገኘትህ /2/
የማይሆንልኝ ነገር የለም /2/
ሁሉ ነው ቀላል /2/ ላመስግንህ
ሁሉ ነው ቀላል /2/

አይቻልምን የሚያስብል ይቻላል
ከባዱን ነገር የሚያደርግ ቀላል
የላዩን እታች የታቹን ላይ
ይህ ህልውናህ ሲያድርግልኝ ሳይ

ኮራሁ ኮራህ ተመካሁ
በአንተ ህልወና ለሞተው
ለሞተው ነገር ሕይወት ነውና /2/

የምፈልገው ሕልውናህን
ነፍሴ የምትሻው መገኘትህን /2/
ከዚያማ ሁሉ ነው ቀላል /4/

ደስ ይላል በህለውናህ መኖር
ደስ ይላል በመገኘትህ መሆን
ደስ ይላል በህልውናህ መኖር
ደስ ይላል በመገኘትህ መሆን

ብርም አይገዛው
ወርቅ የማተካው እርካታ
የሕዝብህ ክብር
የሕዝብህ ሞገስ ነህ ጌታ /2/

አሁንም ደስ አለኝ ስዘምርልህ
አሁንም ደስ አለኝ ሳመሰግንህ /2/

ምስጉን ነህ የተመሰገንህ
ክቡር ነህ እጅግ የከበርክ /2/