Agegnehu Yideg/Yetsion Teguaz Negn/Yetsion Teguaz Negn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

Anten kagagn jamiro Yafssawo samayaw =አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ

ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ
የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት
የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት (፪x)

የፈሰሰው ፡ ሠማያዊ ፡ ፀጋ አኑሮኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋ የመረጥከኝ ፡ ተባረክልኝ የወደድከኝ ፡ ተባረክልኝ

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞተሃል አበሳዬን ፡ ወስደሃል ምን ፡ ልክፈልህ እንዲያው ፡ ልገዛልህ (፪x)

ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው ታሪኬን ፡ ለውጦ ከሞት ፡ አስመልጦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (፪x)

አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ
ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ
የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት
የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት (፪x)

ብዛት የዓለም ፡ ክብር ፡ ሃብት ፡ አያጓጓኝም ከአንተ ፡ አይበልጥብኝም መርጬሃለሁ ፡ እከተልሃለሁ መርጬሃለሁ ፡ እከተልሃለሁ

የምሕረትህ ፡ የፍቅርህ ፡ ብዛቱ አልበርደም ፡ ግለቱ ያዘምረኛል ፡ ተድላየ ፡ ሆኖኛል ያዘምረኛል ፡ ሞገሴ ፡ ሆኖኛል

ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው ታሪኬን ፡ ለውጦ ከሞት ፡ አስመልጦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (፪x)

አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት (፪x)

በመረጥክልኝ ፡ ሕያው ፡ አዲስ ፡ መንገድ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ ልራመድ መጨረሻየ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታየ መጨረሻየ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታየ

የሩቅ ፡ አገር ፡ የጽዮን ፡ ተጛዥ ፡ ነኝ በሰማይ ፡ አገር ፡ አለኝ ታድያለሁ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ ታዲያለሁ ፡ ዘላለም ፡ አርፋለሁ |