Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Weletaw

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ውለታው አልበም ኃይለኛ እንዳንተ የለም

አዝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ

ኢየሱሴ ለእኔ በመስቀል ሞተልኝ ውለታው በዛብኝ በእንጨት ተንጠልጥሎ እርግማን ሆነልኝ ውለታው በዛብኝ በከበረ ደሙ በውድ ዋጋ ገዛኝ ውለታው በዛብኝ ሲጠራኝ ብቻዬን ዛሬ ግን አበዛኝ ውለታው በዛብኝ

ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ

አዝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ

ከበለስ ዛፍ በታች ተቀምጬ አይኝ ውለታው በዛብኝ ተንኮል የሌለብህ የእስራኤል ልጅ አለኝ ውለታው በዛብኝ ታማኝ አድርጐ ቆጥሮ ለአገልግሎት ሾመኝ ውለታው በዛብኝ ኢየሱሴን መጠጋት ለእኔ እጅግ ጠቀመኝ ውለታው በዛብኝ

ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ

አዝ ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ

በግ እረኛ ነብረኩ ገና ብላቴና ውለታው በዛብኝ እግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘሁኝና ውለታው በዛብኝ እኔን በናቁኝ ፊት ራሴን በዘይት ቀባኝ ውለታው በዛብኝ ንጉሡ ሊያከብረኝ ወደ እልፊኙ አገባኝ ውለታው በዛብኝ

ሰው ላደረገልኝ እንደዚህ ዛሬ ሥሙን ላወድሰው በዝማሬ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ (7)

አዝ ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ ውለታው በዛብኝ።