From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኃጥያተኞች ፡ ሳለን ፡ እግዚአብሔር ፡ አሰበን
ከፋንዲያ ፡ ላይም ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አረገን
በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x)
ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
አዕምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ ሰላሙን ፡ ሰጥቶናል
በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ምድር ፡ ብትናውጥ ፡ አንዳች ፡ አንሆንም
የመረጠን ፡ አምላክ/ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አይተወንም (፪x)
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x)
ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
ኢየሱስ ፡ እረኛችን ፡ ጠባቂያችን ፡ ሆኗል
በሞት ፡ ጥላም ፡ ብንሄድ ፡ ምንድን ፡ ያስፈራናል
በለመለምው ፡ መስክ ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ
ሁሌ ፡ ይመራናል ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መንገድ (፪x)
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x)
ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከላይ ፡ በድንቅ ፡ ጐብኝቶናል
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ በእሳት ፡ አጥልቆናል
በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን
እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እንለመልማለን
በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን
በሽምግልናችን ፡ እንለመልማለን
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x)
ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
|