Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Mengedien Adera

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ መንገዴን አደራ ባለፈው ዘመኔስ ብዙ አጥፍቻለው ባለማስተዋሌም ተጎድቻለው ፍቅርን የተሞላህ ባታግዘኝ ኖሮ እንዴት ይዘለቃል የዚህ ምድር ኑሮ

አሁንም ጌታዬ መንገዴን አደራ ታዳጊ አንተ ነህ በሚገጥመኝ መከራ (2)

መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ዘመኔስ ስራህን ስራ (2)

ጉዞዬ ከብዶብኝ ስወድቅ ስነሳ እዚህ ደርሻለው በብዙ አበሳ የቀረው ዘመኔስ ብሩህ ይሁንልኝ ኢየሱሴ በኃይልህ ስራዬን ስራልኝ

የኋላዬን ልርሳ ወዳንተ ልጠጋ ከፊቴ ያለውን ለመያዝ ልዘርጋ

መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ጉዞዬስ ስራህን ስራ(2)

በስጋዬ ምኞት በከንቱ ስገዛ ስንት ጊዜ አቃጠልኩ እንዲሁ በዋዛ ለቅዱሱ አደራህ ታማኝ አልነበርኩም እንደልብህ ደስታም አላገለገልኩም

እንግዲህስ ጌታ ስራብኝ እንደሰው (በጭንጋፉ) በትንሹ ባሪያ ከሁሉም በማንሰው