From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰላሳ ስምንት አመት ባልጋ ላይ ተኝቼ ተኝቼ
ወደ ፈውስ ቦታ የሚያደርሰኝ እንድም ሰው አጥቼ
የነፍሴን መጎዳት ብቸኝነቴን ኧረ ማን አየልኝ ማን አየልኝ
የሱሴ ብቻ ነው የደረሰልኝ ዛሬስ ይብቃህ ያለኝ ይክበርልኝ
ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ
ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2
ማነው ሰላም የሌለው
የሱስን አሁን ይከተለው
ማነው እረፍት የራቀው
የሱስን እኔ ላስተዋውቀው
አስራ ሁለት አመት ከሰው ተገልዬ እጅግ ደም ሲፈሰኝ ሲፈሰኝ
በሽታዬ ላይድን ዝም ብሎ ገንዘብ ሲያስጨርሰኝ
ወደ እየሱስ መጣው ተጋግጬ ጨርቁን ዳሰስኩኝ ዳሰስኩኝ
ሃይልም ከሱ ወጣች እኔም እንደሰው ፈውስ አገኘሁኝ ይክበርልኝ
ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ
ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2
ማነው ሰላም የሌለው
የሱስን አሁን ይቀበለው
ማነው ወዳጅ የራቀው
የሱስን እኔ ላስተዋውቀው
በስምዖን ቤት ውስጥ እንዳለ ወሬ ሰማሁኝ ሰማሁኝ
ከሃጥያት በሽታ ለመዳን ስሮጥ ገባሁን
ከእግሩ ስር ወድቄ ማረኝ አልኩኝ ስቅስቅ እያልኩኝ አለቀስኩኝ
በብዙ ወደድኩት በብዙ ማረኝ ወደ እርሱ አስጠጋኝ ይክበርልኝ
ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ
ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2
ማነው ሰላም የሌለው
የሱስን አሁን ይቀበለው
ማነው ጤና የራቀው
የሱስን እኔ ላስተዋውቀው
በሞት እንቀጣ ተፈርዶብኝ ከጉንይ ሰቅለውኝ ሰቅለውኝ
ይሄ ሰው ፃድቅ ነው ሃጥያት የለበትም ብዬ ተናገርኩኝ
በእውነት እልሃለው ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ አለኝ ነህ አለኝ
እስራኤል አለና ስሜን ለወጠልኝ ከመሞት አዳነኝ ይክበርልኝ
ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ
ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/4
|