Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Kekeber Wede Keber

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ከክብር ወደ ክብር አልበም ኃይለኛ እንዳንተ የለም

ትላንት በእሳቱ ላይ ተራመድን በእግዚአብሔር ፀጋ ሁሉን አለፍን ማዕበል ወጅቡን የገሰፀው የያዕቆብ አምላክ ከእኛ ጋር ነው (፪x) የነሙሴ አምላክ ከእኛ ጋር ነው (፪x)

ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን ኢየሱስን ይዘን ማነው ሚቋቋመን ገና እናብባለን! (፪x)

ደረቁ ስንባል ለመለምን በእግዚአብሔር ታደሰ ኃይላችን ገና በምድር ሁሉ እንበዛለን ወንጌሉን በስልጣን እንሰብካለን (፪x)

ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን ኢየሱስን ይዘን ማነው ሚቋቋመን ገና እናብባለን!(፪x)