Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Haylegna Endante Yelem
ከባርነት አገር ወደ አንተ ያመጣኸን
ቀንበርን ሰባብረህ አርነት ያወጣኸን
በጨለማ ያለ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ
ከሰቆቃ ኑሮ ከሴይጣን ተለየ
አዝ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም
ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ x2
እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም
የሚጤሰውን ጧፍ አጥፍተህ አታውቅም
ለደካማው ኃይልን ለጭንጋፉ ሞገስ
አንተ ግን ጌታ ነህ ለዘለዓለም ንገሥ
አዝ
{ኃይለኛ እንዳንተ የለም
ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ}x2
በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ
ማኅተሙን ሊፈቱ አንዳቸውም አልቻሉ
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ
አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ፡ ልትፈታ
አዝ
{ኃይለኛ እንዳንተ የለም
ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ}x2
ሞተሃል ተብሎ እኛም ተስፋ ቆርጠን
በራችንን ዘግተን አዝነን ተቀምጠን
አንተ ግን ልዩ ነህ ታሪክ ለውጠሃል
ሞትና መውጊያውን ለዘለዓለም ሰብረሃል
አዝ
{ኃይለኛ ፡ እንዳንተ ፡ የለም
ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ}x2
ትዕቢተኛውን ፈርዖን ሊያጠፋን ሲነሳ
ዙሪያችንን ሲዞር ሊውጠን እንደ አንበሳ
ቀድመህ ደረስክና አፉን ለጐምክልን
ምን እንበላ ሌላ ለእኛስ ዘለዓለም ንገሥልን
አዝ
{ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ}
Big text