From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እናምናለን እናምናለን የእግዚአብሔርን ክብር እናያለን
እናምናለን እናምናለን ክዚህም የሚበልጥ አናያለን
እናምናለን እናምናለን ተስፋችን ተፈፅሞ እናያለን
እናምናለን እናምናለን እኛም ተጎብኝተን እናያለን
ወንድማችን ከሞተ አራት ቀኑ ሆነው
ጌታን እንጠብቃለን ነገር ሁሉ ለበጎ ነው
እርሱ ግን በጊዜው ይመጣል
አላዛር ከመቃብር የወጣል
የሱስ ግን በጊዜን ይመጣል
የሞተው ከበቃብር ይወጣል
እናምናለን እናምናለን የሞተው ተነስቶ እናያለን
እናምናለን እናምናለን እኛም ታስበን አናያለን
የመጐብኛችን ቀን ደርሶ
የእግዚአብሔር ኃይል ከላይ ወርዶ
ልመናዋ ተሰምቶላት ለመበለቲቱ ተፈርዶ
እናያለን ገና በጌታ
ጥማት ተለውጦ በእርካታ
እናያለን ብዙ በጌታ
ያስቸገረን ሁሉ ሲፈታ
እናምናለን እናምናለን መሃተም ሲፈታ እናያለን
እናምናለን እናምናለን ስድባችን ተወግዶ አናያለን
ለሰዎች ጥያቄ ሆነን
እስከ መቼ እንኖራለን
በስውር የለመንነውን
በግልፅ እንቀበላለን
መቼ እንዳለቀሰች ትቀራለች
ሃናም ሳሙኤልን ትወልዳለች/2
እናምናለን እናምናለን መካሪቱ ወልዳ እናያለን
እናምናለን እናምናለን አዲስን ነገር አናያለን
የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ
ማነው በፊቱ የሚቆመው
አጋንንት ኃጢአት በሽታ
ይወገዳሉ ፈፅመው
የታሰሩት ሁሉ ይፈታሉ
ለአምላካቸው ክብርን ይሰጣሉ
አመፀኞች ሁሉ ይማረካሉ
ለኢየሱሴ ክብር ይሰግዳሉ
እናምናለን እናምናለን ወንጌላችን ተዳርሶ እናያለን
እናምናለን እናምናለን ከዚህም የሚበልጥ አናያለን
እናምናለን እናምናለን ሽባ ሲተረተር እናያለን
እናምናለን እናምናለን እውራን ሲበሩ አናያለን
እናምናለን እናምናለን እኛም ተጎብኝተን እናያለን
እናምናለን እናምናለን ከዚህም የሚበልጥ አናያለን
ጎዶሏችን ሞልቶ አናያለን
ከዚህም የሚበልጥ አናያለን
እኛም ተጎብኝተን አናያለን
ሸለቋችን ሞልቶ አናያለን
ሳራም ታስባ አናያለን
እኛም ተጎብኝተን አናያለን
|