From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ዲያቢሎሰን ተቃወሙት ከናንትም ይሸሻል
ወደ እግዚያብሔሀር ቅረቡ ወደ እናንተ ይቀርባል
በጸሎት ፅኑ ሁል ጊዚ አሳስቡት
የሚያስጨንቃችሁን በእርሱ ላይ ጣሉት
ወገኖች ወገኖች በርቱ በርቱ
ለሰይጣን ሽንገላ እንዳትረቱ እንዳትረቱ
ዘመኑ እጅገ ክፉ ቢሆንም
መከራን ታገሱ ጌታ አይተወንም
ሳትታክቱ ዘወትር ፀልዩ
ከመስቀሉ ስር አትለዩ
ወገኖች ወገኖች በርቱ በርቱ
ለሰይጣን ሽንገላ እንዳትረቱ እንዳትረቱ
መጋደላችን ከሰይጣን ጋር ነዉ
ሃሳቡን አትሳቱ የሃሰት አባት ነው
በሃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ
በእምነት ተጋደሉ በሃይማኖት ፅኑ
ወገኖች ወገኖች በርቱ በርቱ
ለሰይጣን ሽንገላ እንዳትረቱ እንዳትረቱ
ወንጌልን ላልሰሙ ወንጌልን አዳርሱ
የዲያቢሎስን ስራ በእየሱስ ስም አፍርሱ
እባብና ጊንጡን በስጣልን ተጫሙ
እርስ በእርስ ተፅናኑ ተሸካከሙ
ወገኖች ወገኖች በርቱ በርቱ
ለሰይጣን ሽንገላ እንዳትረቱ እንዳትረቱ
ከትላንት ይልቅ ዛሬ መዳናችን ቀርቦል
በርቱና ተዋጉ ዲያቢሎስ ተዋክቦአል
የቃሉን ሰይፍ ያዙ የእምነት ጋሻ አንሱ
እየሱስ ጌታ ነው ይህንን አትርሱ
ወገኖች ወገኖች በርቱ በርቱ
ለሰይጣን ሽንገላ እንዳትረቱ እንዳትረቱ
|